Skip to main content

የገንዘብ እርዳታ ፖሊሲ Financial Aid Policy, Amharic (Ethiopia)

ርዕስ፦    
የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲ        
ቀን፦ 1/21/2025
            
በዚህ ቀን የታተመውን 
እትም ይተካል፦ 6/3/2024

ምድብ፦    
SYS.MIS.FAP    
ገጽ 1 ከ 12    
የጸደቀው በ፦    
UVACH Inc. ቦርድ
 

ፖሊሲ

ይህ የUVA Community Health (UVACH) ፖሊሲ ሲሆን፣ ይኽም አስፈላጊ የጤና ክብካቤን ለሁሉም ለማዳረስ፣ UVA Health Culpeper Medical Center (CPMC)፣ UVA Health Haymarket Medical Center (HAMC)፣ UVA Health Prince William Medical Center (PWMC)፣ UVACH Medical Group፣ እና UVA Health Cancer Center Gainesville ያካትታል። UVACH ከሚገቡበት ጊዜ ጀምሮ፣ አገልግሎት እስከሚያገኙበት እና ታክመው እስከሚወጡበት፤ እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያ እስከሚጠየቁበት እና የገንዘብ መሰብስብ ሂደቶች እስከሚከናወኑበት ጊዜ ድረስ ታካሚዎችን፣ መድን ያላቸውንም ሆነ የሌላቸውን፣ በአግባቡ፣ በአክብሮት እና በአዛኝነት ያስተናግዳል። ይህ ፖሊሲ የተረቀቀው በ1986 Internal Revenue Code Section 501(r) ውስጥ የተጠቀሱ ግዴታዎች፣ የገንዘብ ድጋፍ እና የድንገተኛ ሕክምና ፖሊሲዎችን፣ ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ የሆኑ ሰዎች ላይ ስለሚኖርይ የክፍያ ገደቦች፣ እንዲሁም ምክንያታዊ የክፍያ መጠየቅ እና መሰብሰብ ጥረቶችን አስመልክቶ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ለማሟላት ታስቦ ነው፤ ስለሆነም በዚያ አግባብ መተርጎም አለበት።

ተፈጻሚነት

ይህ ፖሊሲ በሁሉም የUVACH የድንገትኛ ክብካቤ ተቋሞች አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን፣ በምርጫ የሚከናወኑ አሰራሮችን አያካትትም።

ብያኔዎች

በአጠቃላይ ተከፋይ መጠኖች (Amounts Generally Billed, AGB)፦ በአጠቃላይ የተጠየቁ መጠኖች ማለት እንዲህ ላሉ አገልግሎቶች መድን ያላቸው ታካሚዎች ለድንገተኛ ሕክምና እና ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች በአጠቃላይ የሚጠየቁት መጠን ነው። የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ የሆኑ ታካሚዎች የሚጠየቁት ክፍያ እንዲህ ላሉ አገልግሎቶች በአጠቃላይ ተከፋይ መጠኖች ("AGB") ያልበለጠ መሆን አለበት። እነዚህ ክፍያዎች ከኖቬምበር እስከ ኦክቶበር ባሉት የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ከMedicare፣ BCBS እና የንግድ ከፋዮች ለድንገተኛ ጊዜ እና ሌሎች ለህክምና አስፈላጊ የሆኑ የይገባኛል ጥያቄዎች በተፈቀደው አማካኝ መጠን ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የተፈቀዱት መጠኖች መድን አቅራቢው የሚከፍለውን መጠን እና ግለሰቡ በግል መክፈል ያለበት መጠን ካለ እርሱንም ያካትታል። የመጨረሻው ስሌት የሚወሰነው ለእነዚህ የይገባኛል ጥያቄዎች ከፋዮች የሚከፍሉትን ዋጋ በጠቅላላ ክፍያዎች በማካፈል ነው። UVACH AGBs በ 26 CFR §1.501(r) ያለፈውን የማየት ዘዴን በመጠቀም ይሰላሉ። የAGB ቅናሽን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አባሪ Aን ይመልከቱ።

ንብረቶች - እርስዎ ያለዎት ጠቅላላ ዋጋ፣ የባንክ እና የጡረታ ሂሳቦችን፣ ቤት፣ መኪና፣ ወዘተ ጨምሮ። በተጨማሪም፣ ተቆጣሪ ንብረቶች የተሸጠ መሬት ዋጋ (የእርሻ መሬትን ጨምሮ)፣ በመዝናኛ ተሽከርካሪዎች፣ ጀልባዎች፣ ሁለተኛ ቤት ወዘተ ላይ ያለዎ የባለቤትነት ድርሻ። ለገንዘብ ድጋፍ ስሌት የሚካተቱ ንብረቶች ከ$50,000 በታች የሆነ መጠን ብቻ ነው።

የተበላሸ ዕዳ - መሰብሰብ እንደማይችሉ ተቆጥረው የተሰረዙ ያልተከፈሉ ገቢዎች፤ ነገር ግን እንደ ተከፋይ ዕዳ ተመዝግበው ያሉ።

የውበት - ዋና ዓላማው አካላዊ ውበትን ማሻሻል የሆነ ቀዶ ጥገና።

ተመጣጣኝ ያልሆነ ድርሻ የወሰደ ሆስፒታል (Disproportionate Share Hospital, DSH) - ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለ ዝቅተኛ-ገቢ ታካሚዎችን የሚያገለግል እና መድን ለሌላቸው ታካሚዎች ላቀረባቸው አገልግሎቶች ክፍያዎችን ከMedicaid እና Medicare አገልግሎት ማዕከላት የሚቀበል።

የተፈቀዱ አገልግሎቶች - በUVACH ተቋማት የሚቀርቡ፣ በዚህ የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲ መሰረት የተፈቀዱ አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  1. በድንገተኛ ሕክምና ክፍል ውስጥ የሚሰጡ ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎቶች።
  2. ድንገተኛ የሕክምና ክፍል ባልሆነ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ለሕይወት አስጊ የሆኑ ክስተቶችን ለመቀልበስ የሚቀርቡ የሕክምና አገልግሎቶች።
  3. ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች።

ድንገተኛ የሕክምና ሁኔታ - አንድ አማካይ የጤና እና ሕክምና የእውቀት ደረጃ ያለው ምክንያታዊና መደበኛ ሰው፣ በአፋጣኝ ሕክምና ካልተገኘ የሚከተሉትን ያስከትላል ብሎ ሊገምተው የሚችለው፣ በበቂ ደረጃ ከባድ በሆኑ የህመም ምልክቶች (ከባድ ህመምን ጨምሮ) እራሱን እየገለጸ ያለ የጤና ሁኔታ-

  1. ለአንድ ግለሰብ ሕይወት አስጊ ሁኔታ፣ ወይም ነፍሰ ጡር ከሆነች፣ የሴቲቱ ወይም የሕጻኑ ሕይወት አደጋ ላይ ሲሆን፤ ወይም
  2. በከባድ ሁኔታ የሰውነት አካላት ሥራ መዛባት፤ ወይም
  3. የማንኛውም የሰውነት ብልት ወይም የሰውነት አካል በከባድ ሁኔታ የተግባር መዛባት።

መደበኛ አልሆነ የመሰብሰብ እርምጃዎች (Extraordinary Collection Actions, ECA)፦ በሆስፒታል ተቋም፣ በተቋሙ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም ለተሸፈኑ አገግሎቶች ክፍያን ከመቀበል ጋር በተያያዘ በግለሰብ ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች

የቤተሰብ ገቢ - አንድ ግለሰብ በደመወዝ ወይም በሌላ መንገድ የሚያገኘው ጠቅላላ የጥሬ ገንዘብ ወይም ተመጣጣኝ ክፍያ። እንደ ገቢ የማይቆጠሩ ነገሮች፣ ጥሬ ገንዘብ ያልሆኑ ድጋፎች እና የሕዝብ ድጋፍ፣ ለምሳሌ የምግብ እና የመኖሪያ ቤት ድጎማዎች፣ እንዲሁም የትምህርት ድጋፍ ናቸው።

የፌዴራል የድህነት መመሪያዎች - የፌዴራል የድህነት ወለል፣ የአንድን ታካሚ እና የእርሷን/ሱን ቤተሰብ የድህነት ወለል፣ ለዚህ ፖሊሲ ዓላማ ሲባል ለመለየት በዩኤስ መንግስት አገልግሎት ላይ ይውላል። የሚመሰረተው በቤተሰቡ አጠቃላይ ሃብት ላይ፣ ዓመታዊ ፍጆታ፣ ወይም የራሳቸው የደህንነት ግምገማ ላይ ሳይሆን በጥሬ ገንዘብ ገቢ ላይ ነው። የድህነት መመሪያዎች በዩኤስ መንግስት የጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎቶች (U.S. Department of Health and Human Services)፣ እንዲህ አይነቶቹ ብያኔዎች በሚኖሩ ጊዜ በፌዴራል መዝገብ ላይ በየዓመቱ ይታደሳሉ።

ወጥ ክፍያ ያላቸው - ለአንዳንድ ታካሚዎች ለሚመርጧቸው አገልግሎቶች፣ አገልግሎቱ በሚሰጥበት ጊዜ በታካሚው የሚከፈሉ ቀድመው የተተመኑ ክፍያዎች።

ከፋይ - ታካሚው፣ ሕክምና አቅራቢው፣ ወይም ለጤና ሕክምና ክፍያ ኃላፊነት ያለበት አካል።

አባወራ - በግብር መግለጫ ላይ "አባወራ" ተብሎ የተገለጸው ሰው።

ቤት አልባ - በጎዳና ላይ፣ በመጠለያ፣ በተተወ ሕንጻ ወይም ተሽከርካሪ፣ ወይም ሌላ መደበኛ ወይም ቋሚ ባልሆነ ቦታ ውስጥ የሚኖር ግለሰብ። ግለሰቡ ከተከታታይ ጓደኞች እና/ወይም ከ90 ቀናት በላይ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ጋር "በእጥፍ ከተጨመረ" አንድ ግለሰብ ቤት እንደሌለው ሊቆጠር ይችላል

የቤተሰብ አባላት ("ጥገኞች") - በቤተሰቡ ውስጥ "የሚኖሩ"፣ በአባወራው የግብር መግለጫ ላይ የታወጁ ግለሰቦች።

የሕክምና ብቁነት አቅራቢ/የሕክምና ድጋፍ አራማጅ - ታካሚዎችን ለመንግስት ፕሮግራሞች እና ለUVACH የገንዘብ ድጋፍ ቅድመ ልየት እንዲያካሂድ ከUVACH ጋር ውል የገባ አራማጅ አቅራቢ።

ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች - አንድን ሕመም፣ ጉዳት፣ ሁኔታ፣ በሽታ፣ ወይም ምልክቶቹን ለመከላከል፣ ለመመርመር፣ ወይም ለማከም የሚያስፈልጉና ተቀባይነት ያላቸውን የሕክምና ደረጃዎች የሚያሟሉ የጤና-ክብካቤ አገልግሎቶች። ከእነዚያ ሁኔታዎች ማንኛውም፣ ሁኔታው አካላዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ምልክቶችን ወይም የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያስከትል ከሆነ፣ ይኽም ለደህንነት ስፈላጊ ሕክምና እንደሆነ የቆጠራል።

መስፈርቱን የማያሟሉ አገልግሎቶች - የሚከተሉት የጤና ክብካቤ አገልግሎቶች በዚህ ፖሊሲ መሰረት ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ አይደሉም፦

  1. ድንገተኛ አደጋ ላስከተላቸው ውጤቶች የሚቀርቡ አገልግሎቶች። እነዚህ ክፍያዎች የሶስተኛ ወገን ባለ ዕዳ ክፍያን ለማረጋገጥ ለተቀመጡ የሕግ መሳሪያዎች፣ እነዚህ መሳሪያዎች ከመጀመሪያ ታካሚው የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም (Patient Financial Assistance Program) መነሻ ብቁነቱ ከመጽደቁ በፊት የተመዘገቡ ቢሆንም እንኳ፣ ተገዥዎች ናቸው። የሶስተኛ ወገን ሽፋን ያለ ከሆነ፣ UVACH ቀሪውን ሂሳብ ከሶስተኛው ወገን ከፋይ ይሰበስባል። ከመድን በኋላ ቀሪ ሂሳብ በሚኖር ጊዜ፣ ታካሚው ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላል። በገቢ እና የገንዘብ ምንጭ ወለል ውስጥ ያሉ ($50,000 ወይም ከዚያ በታች በሆነ ንብረት ከድህነት መመሪያዎች 400% በታች የሆኑ) መድን ያላቸው ታካሚዎች፣ በመድን ኩባንያው እና በUVACH መካከል ካለው ውል ጋር የማይጋጭ እስከሆነ ድረስ፣ ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ።
  2. ለህክምና አስገዳጅ ያልሆኑ በምርጫ የሚወሰዱ አሰራሮች፣ ለምሳሌ የውበት ማሻሻያ እና ወጥ ክፍያ ያላቸው አሰራሮች፣ እንዲሁም መድናቸውን መጠቀም የማይፈልጉ መድን ያላቸው ታካሚዎች፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል የሕክምና መሳሪያ፣ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ማድረጊያ እና በሐኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶች።
  3. ከግዛት ውጪ ያለ Medicaidን ጨምሮ ግን በእሱ ብቻ ሳይገደብ UVA የእርስዎ መድን ላይ ካልተሳተፈ ወይም የመድን ይገባኛል ጥያቄዎች ከአውታረ መረብ ውጪ እንደሆኑ ከታሰቡ የገንዘብ ድጋፍ አይተገበርም። 

ሕጋዊ ግዴታዎች

ይህን ፖሊሲ በመተግበር UVACH፣ ይህን ፖሊሲ ለማስፈጸም በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ሁሉ፣ ሁሉንም የፌዴራል፣ የግዛት እና አካባቢያዊ ሕጎችን፣ ደንቦችን፣ እና መመሪያዎችን ማክበር አለበት።

አሰራር

ለዚህ አሰራር ምክንያቱ፣ UVACH ለፌዴራል እና ግዛት ወይም አካባቢያዊ የጤና መድን ፕሮራሞች ወይም ለUVA የማኅበርሰብ ጤና ታካሚ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም ("FAP") ብቁ የሆኑ ግለሰቦችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመለየት ቅድመ ልየታ ማድረጉ ነው። በማንኛውም ግለሰብ ላይ የዚህ ፖሊሲ ትግበራ የሚከናወነው ለገንዘብ ድጋፍ የሚያቀርቡት ማመልከቻ ከሁሉም አስፈላጊ ሰነዶች ጋር ቀርቦ ማመልከቻው አጥጋቢ በሆነ መልኩ ሲጠናቀቅ ነው። የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻውን፣ ደጋፊ ሰነዶችን ጨምሮ፣ አጥጋቢ በሆነ መልኩ ለማሟላት ያልቻለ ታካሚ፤ በዚህ ፖሊሲ መሰረት ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ አይሆንም (ይኽም በደንብ Section 501(r) ሥር ባለው መመሪያ መሰረት ታካሚው ማሳወቂያዎች ደርሰውት ከሆነ ነው)። መረጃው ወይም ሰነዱ በFAP ወይም በFAP ቅጽ ውስጥ የተብራራ ካልሆነ በስተቀር፣ አመልካቹ ያንን መረጃ ባለማቅረቡ ምክንያት UVACH በFAP መሰረት የገንዘብ ድጋፍ ሊከለክል አይችልም። ታካሚዎች የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ አባሪ Bን ይጠቀሙ።

UVACH ለድንገተኛ የሕክምና ፍላጎት እና/ወይም በምጥ ላይ ላሉ ነፍሰ ጡሮች፣ ለFAP ብቁ ሆኑም አልሆኑ ያለ አድልዎ አገልግሎት ያቀርባል። UVACH ግለሰቦች ለድንገተኛ ሁኔታ የሕክምና እርዳታ እንዳይጠይቁ የማያበረቱ ማናቸውም ድርጊቶች ውስጥ አይሳተፍም፤ እንዲሁም ታካሚውን ስለ መድን ወይም የክፍያ ሁኔታ በመጠየቅ ማንኛውም የምርመራ እና የሕክምና ሂደት እንዳይዘገይ የሚከለክል የድንገተኛ የህክምና እንክብካቤ እና የሰራተኛ ህግ (The Emergency Medical Treatment and Labor Act, EMTALA) ፖሊሲ አለው። የUVACH EMTALA ፖሊሲ በተጨማሪም ከሌሎች ተቋማት የሚተላለፉ ድንገተኛ የጤና ሁኔታ ያለባቸውን ታካሚዎች መቀበያ አሰራሮች አሉት።

UVACH ሁሉም ታካሚዎች፣ ለUVACH FAP ቅድመ ልየታ ከመካሄዱ በፊት፣ ለፌዴራል፣ ግዛት ወይም አካባቢያዊ የመድን ፕሮግራሞች ቅድመ ልየታ እንዲከናወንላቸው ይጠብቃል። FAP ለግል ኃልፊነት መተኪያ መሆን ስለማይችል፣ በፕሮግራሙ ስር FA የሚፈልጉ ሰዎች፣ ብቁነትን ለመለየት በሚሰራው ሥራ፣ እንዲሁም አቅማቸው እስከሚፈቅደው ድረስ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ አስተዋጽዖ ለማበርከት ከUVACH አሰራሮች ጋር እንዲተባበሩ ይጠበቃል። ታካሚዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ለUVACH ተገቢ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል። የጤና መድን ለመግዛት አቅማቸው የሚፈቅድላቸው ግለሰቦች፤ የጤና ክብካቤ አገግሎትን በስፋት ለማዳረስ እንዲረዳ እንዲሁም ለእራሳቸው ግላዊ ጤና አጠባበቅ ያንን እንዲያደርጉ ይበረታታሉ። አንድ ታካሚ ለአንድ የተወሰነ አሰራር ወይም የአገልግሎት ቀን ከመድን ሽፋኑ ክፍያ መጠየቅ ካልፈለገ፣ ያ ጉብኝት ለFAP ብቁ አይሆንም።

በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ተፈጻሚነት ያለው የግዛት ሕግ፣ በእነዚህ ግዛቶች ውስጥ ባሉ በሆስፒታሎች ላይ ተጨማሪ ወይም የተለዩ ግዴታዎችን ሊጥል ይችላል። የዚህ ፖሊሲ ዓላማ፣ እንዲህ አይነት ግዛቶች ውስጥ የፌዴራል እና የግዛት ሕጎችን፣ ሁለቱንም ማክበር ነው። ስለሆነም፣ አንዳንድ ድንጋጌዎች ከዚህ በታች እንደተገለጸው ተፈጻሚ የሚሆኑት በአንዳንድ ግዛቶች ነው።

  1. የብቁነት መስፈርቶች

UVACH የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎቶችን ለማንኛውም አገልግሎቱን ለሚፈልግ ግለሰብ ያቀርባል፤ እንዲሁም በማንኛውም ሰው ላይ፣ በመክፈል አቅም ላይ በመመስረት፤ ወይም ለእነዚያ አገልግሎቶች የሚከፈለው በMedicare፣ በMedicaid፣ ወይም በCHIP ላይ መሆኑ ላይ ተመስርቶ፤ በግለሰቡ ዘር፣ ጾታ፣ የትውልድ አገር፣ የአካል ጉዳት፣ ኃይማኖት፣ እድሜ፣ የጾታ ዝንባሌ፣ ወይም የጾታ ማንነት ላይ በመመርኮዝ አያገልልም፣ ድጎማዎችን አይከለክልም፣ ወይም በሌላ በማንኛውም መልኩ አድልዎ አያደርግም። 

  1. ታካሚዎችይ እሚከፍሏቸው መጠኖች

FAP፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ አገልግሎቶች፣ መድን ላላቸውም ሆኑ ለሌላቸው፣ የቤተሰብ ገቢያቸው፣ በዓመታዊ አማካይ እና ንብረታቸው ከ$50,000 ወይም ከዚያ በታች የሆነና፣ ከወቅቱ የፌዴራል የድህነት መመሪያዎች (Federal Poverty Guidelines, FPG) 200% የሆነ የቤተሰብ ገቢ ላላቸው ታካሚዎች፣ በዚህ ፖሊሲ ውስጥ በተበየነው መሰረት 100% የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። UVACH በተጨማሪም የቤተሰብ ጠቅላላ ገቢ ከFPL 201% እና 400% መካከል ሆነው ንብረታቸው ከ$50,000 ለሆኑ ታካሚዎች ቅናሽ ተመን ያቀርባል። (አባሪ C)።

  1. AGB

ለFAP ብቁ የሆነ ግለሰብ ለድንገተኛ እና ሌሎች ለደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ሕክምናዎች ከAGB በላይ እንዲከፍል አይጠየቅም። UVACH AGB በየዓመቱ እንደ ገበያው ሁኔታ የሚሰተካከል ሲሆን የሚሰላውም፣ የጋራ-ክፍያዎችን እና ተቀናሾችን ጨምሮ የMedicare እና የንግድ ተመኖችን ወደ ኋላ በመመልከት ዘዴ ነው (አባሪ D)። UVACH በተጨማሪም የመድን ሽፋን ለሌላቸው እና ለገንዘብ ድጋፍ መስፈርቱን ለማያሟሉ ታካሚዎች በራስ የሚከፈል ቅናሽ ያቀርባል።

  1. የብቁነት የጊዜ ገደብ

ታካሚዎች ከመጀመሪያው የክፍያ መጠየቂያ መግለጫ ቀን ጀምሮ ባሉት 240 ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ። ታካሚው ለገንዘብ ድጋፍ ፈቃድ ካገኘ ሽፋናቸው፣ ከማመልከቻ ማፅደቂያው ቀን ጀምሮ ለ5 ዓመታት ወደኋላ እና ለ365 ቀናት ወደፊት ያገለግላል። ፈቃድ በተሰጠበት የ240 ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ አገልግሎት ለማግኘት የሚመለሱ የገንዘብ ድጋፍ የተፈቀደላቸው ታካሚዎች ለፌዴራል፣ ለግዛት እና ለአካባቢያዊ የመድን ፕሮግራሞች በእያንዳንዱ ጉብኝት ማጣሪያ ምርመራ ይከናወንላቸዋል። የUVACH የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮግራም (UVACH financial assistance program) አይደለም።

  1. ተሳታፊ አቅራቢዎች

አንዳንድ ለደህንነት አስፈላጊ የሆኑ እና የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የUVACH ሰራተኞች ያልሆኑ የUVACH ባልሆኑ አቅራቢዎች ይቀርባሉ፤ እነዚህም ይህን የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲ ያልተቀበሉ እና የተለየ የክፍያ ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ሊሆኑ ይችላሉ። ድንገተኛ ወይም ሌላ ለህክምና አስፈላጊ የሆኑ እንክብካቤዎችን የሚሰጡ እና የUVACH የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራምን ያልተቀበሉትን ሙሉ የአቅራቢዎች ዝርዝርን በተመለከተ ለዝርዝሮች አባሪ Eን ይመልከቱ።

የአሰራር መመሪያዎች

ለአሰራር መመሪያዎች አባሪ Fን ይመልከቱ።

ይህ ፖሊሲ በUVACH የዲሬክተሮች ቦርድ የጸደቀ ነው።

ለክፍያ መጠየቅ እና መሰብሰብ የእኛን የክፍያ መጠየቅ እና መሰብሰብ ፖሊሲ ይመልከቱ።

 

(አባሪ A)።

የUVA Health Culpeper Medical Center (CPMC) AGB ቅናሽ

የAGB ቅናሾችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ለደንበኞች አገልግሎት በስልክ ቁጥር 540-829-4320 or 540-829-4330 (የአገር ውስጥ) በመደወል ማግኘት ይቻላል 

UVA Health Haymarket Medical Center AGB ቅናሽ 

የAGB ቅናሾችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ለUVA Haymarket Medical Center (HAMC) በመደወል ማግኘት ይቻላል፦ 571-284-1517

UVA Health Prince William Medical Center (PWMC)፦ የAGB ቅናሽ 

የAGB ቅናሾችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ለ UVA Prince William Medical Center (PWMC) በመደወል ማግኘት ይቻላል። 703-369-8020

 

አባሪ B

የገንዘብ ድጋፍ መረጃ ማግኘት

ታካሚዎች የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻውን ከhttps://uvahealth.com/services/billing-insurance/financial-assistance-eligibility ከምዝገባ ክፍል፣ ወይም በሆስፒታል ተቋሞች ውስጥ ከሚገኘው የገንዘብ አማካሪ ወይም ለደንበኞች አገልግሎት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ማግኘት ይቻላል፦

UVA Health Culpeper Medical Center (CPMC)፦ 540-829-4320 or 540-829-4330 (የአገር ውስጥ) 

UVA Health Haymarket Medical Center (HAMC)፦ 571-284-1517

UVA Health Prince William Medical Center (PWMC)፦ 703-369-8020

 

አባሪ C

UVA HEALTH CULPEPER MEDICAL CENTER (CPMC) ማስተካከያ መቶኛዎች

 

ንብረቶች

<=200% FPL

201%-300% FPL

301%-400% FPL

ቅናሽ

<=$50,000

100%

85%

75%

 

UVA HEALTH HAYMARKET MEDICAL CENTER (HAMC) ማስተካከያ መቶኛዎች

 

ንብረቶች

<=200% FPL

201%-300% FPL

301%-400% FPL

ቅናሽ

<=$50,000

100%

85%

75%

 

UVA HEALTH PRINCE WILLIAM MEDICAL CENTER (PWMC) ማስተካከያ መቶኛዎች

 

ንብረቶች

<=200% FPL

201%-300% FPL

301%-400% FPL

ቅናሽ

<=$50,000

100%

85%

75%

 

UVACH MEDICAL GROUP ማስተካከያ መቶኛዎች

 

ንብረቶች

<=200% FPL

201%-300% FPL

301%-400% FPL

ቅናሽ

<=$50,000

100%

85%

75%

 

አባሪ D

በአጠቃላይ ተከፋይ መጠኖች

 

AGB

UVA HEALTH CULPEPER MEDICAL CENTER (CPMC)

 

36%

UVA HEALTH HAYMARKET MEDICAL CENTER (HAMC)

34%

UVA HEALTH PRINCE WILLIAM MEDICAL CENTER (PWMC)

39%

አባሪ E

ተሳታፊ አቅራቢዎች

የድንገተኛ ሕክምና እና ሌሎች ለደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ሕክምናዎችን የሚሰጡ፣ ነገር ግን የUVACH የገንዘብ ድጋፍን ያልተቀበሉ ሐኪሞችን ሙሉ ዝርዝር ለማግኘት፣ የሚከተለውን ድር ጣቢያ ይጎብኙ፦ 

https://uvahealth.com/services/billing-insurance/financial-assistance-information

 

አባሪ F

የአሰራር መመሪያዎች

እነዚህ መመሪያዎች ሰራተኞች የዚህን ፖሊሲ ግቦች ለማሳካት እንዲረዳቸው የተቀመጡ መመሪያዎች ናቸው። እነዚህን የአሰራር መመሪያዎች ሲከተሉ፣ ሰራተኞች በራሳቸው የሥራ ድርሻ እና ኃላፊነት ውስጥ ባሉ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ግምት እንዲወስዱ ይጠበቅባቸዋል።

የብቁነት ሂደት

ለገንዘብ ድጋፍ ብቁነትን ለመለየት የሚከተሉት ሂደቶች አገልግሎት ላይ ይውላሉ፦

  1. አንድ ማመልከቻ ተሞልቶ እና በታካሚው ወይም ሥልጣን በተሰጠው ወኪል ይፈረማል። የማመለቻው ዓላማ የአንድን ታካሚ ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ መሆን አለመሆኑን ለመለየት የሚያስፈልገውን መረጃ መመዝገብ ነው።
  2. ውጫዊ የመረጃ ምንጮች በታካሚው ወይም በታካሚው ዋስ የመክፈል አቅምን ለመገምገም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ (ለምሳሌ የክሬዲት ስኮር)
  3. ታካሚዎች ለገንዘብ ድጋፍ ለማመልከት ቀሪ ሂሳብ ወይም ቀጠሮ የተያዘለት አገልግሎት UVACH ዘንድ ሊኖራቸው ይገባል ብቁነት ገቢ አሰባሰብ ዑደት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ሊወሰን ይችላል።
  4. ከሕክምና ብቁነት አቅራቢዎቻችን ጋር የማይተባበሩ ታካሚዎች በዚህ ፖሊሲ መሰረት ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ አይደሉም።
  5. ተጨማሪ መረጃ ከተፈለገ፣ ጥያቄው ለገንዘብ ድጋፍ አመልካቹ በፖስታ መልዕክት እንዲደርሰው ይደረጋል። ደብዳቤው ታካሚው መረጃውን በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያቀርብ ይመክራል። የተጠየቀው መረጃ በ30 የሥራ ቀናት ውስጥ ካልቀረበ የአመልካቹን የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ በተመለከተ ምንም ተጨማሪ ሥራ አይከናወንም።
  6. የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ በፍጥነት ምላሽ ያገኛል፣ UVACH ጥያቄው መፈቀዱን ወይም አለመፈቀዱን፣ ማመልከቻውን ለማሟላት የተጠየቁ ሁሉንም ሰነዶች ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ለአመልካቹ ለማሳወቅ ምክንያታዊ ጥረት ያደርጋል።

ገቢን ማረጋገጥ፣ ንብረቶች እና የገንዘብ ምንጮች

የሚከተሉት ሰነዶች የአንድን ቤተሰብ ገቢ ለማረጋገጥ አገልግሎት ላይ ሊውሉ ይችላሉ፦

  1. የታካሚው ቤተሰብ የቅርቡ የካላንደር ዓመት የግብር ማሳወቂያ።
    • ታካሚው የራሱን ሥራ የሚሰራ ከሆነ፣ የታካሚው የመጨረሻው ሩብ ዓመት የንግድ ፋይናንስ ሂሳብ መግለጫዎች ካለፈው ዓመት የግብር ማሳወቂያ ጋር፣ እድኒሁም የታካሚው የግል የግብር መግለጫ።
  2. የቅርብ ጊዜዎቹን ሶስት የክፍያ ቲኬቶች ከአሰሪዎች።
  3. ክልከላን ወይም ብቁነትን የሚያሳይ እንዲሁም የተቀበሉትን መጠን የሚያሳይ ወቅታዊ የሥራ አጥነት ወይም የሰራተኛ ካሳ ድጎማዎች ደብዳቤ
  4. ወቅታዊ የማኅበራዊ ደህንነት ደብዳቤ፣ የአካል ጉዳት ማሳወቂያ ደብዳቤ፣ ወይም ሙሉ የባንክ ሂሳብ መግለጫ ለማኅበራዊ ደህንነት ቀጥታ ተቀማጭ።
  5. ወቅታዊ የጡረታ መግለጫ።
  6. SNAP ደብዳቤ።
  7. በፍርድ ቤት የታዘዘ ደብዳቤ ወይምየልጅ ድጋፍ ተቆራጭ መጠን የሚያመለክት አሳዳጊ ካልሆነ ወላጅ የተገኘ ደብዳቤ።
  8. ጠቅላላ የኪራይ ገቢን የሚያመለክት የኪራይ ውል ስምምነት ወይም ሰነድ።
  9. ማናቸውንም ስቶክ፣ ቦንድ፣ ሲዲዎች፣ የጤና ቁጠባ ሂሳቦችን (Health Savings Accounts, HSA’s) ዝርዝር የያዘ፣ ወይም ሌሎች ማንኛውንም ተጨማሪ ንብረት የሚያመለክት ሰነድ።
  10. ማንኛውንም አሁን ያለዎትን የቼኪንግ፣ የቁጠባ፣ የገንዘብ ገበያ ሂሳቦች ሙሉ ዝርዝር የያዘ ቅጅ።

ሌሎች ገቢዎች ወይም የንብረት ገቢ ምንጮች, ተቀማጮች፣ ከቼኪንግ፣ እና የጡረታ ሂሳቦች እንዲሁም የተቀማጭ ሰርቲፊኬቶች (Certificates of Deposit, CDs) ጨምሮ ይገመገማሉ። የጤና ቁጠባ ሂሳቦች (HSA’s) ይገመገማሉ፤ ማንኛውም የገንዘብ ድጋፍ አቅርቦት ከመፈቀዱ በፊት፣ ማናቸውም ገንዘቦች በጤና ክብካቤ ወጬዎች ላይ መዋል አለባቸው። ሁሉም የቤተሰብ አባላት የባንክ ሂሳቦች ይጠየቃሉ። አመልካቹ እነዚህን ሰነዶች ካላቀረበ፣ UVACH ተጨማሪ መረጃ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለአመልካቹ ይልካል። ማንኛውም ሰነድ ላልቀረበ፣ የገንዘብ ድጋፍ ይከለከላል።

ምንም እንኳ፣ ለታካሚው የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም ሲባል የገቢ ማረጋገጫ ቢጠየቅም፣ አንዳንድ የአካባቢ ሥርዓት DHS መመሪያዎች የገቢ ማረጋገጫ ሊጠይቁ ይችላሉ። በአካባቢያዊ ሥርዓት የDSH ፕሮግራሞችን ለማክበር፣ እንዲህ አይነቶቹ መመሪያዎች እንደየጉዳዩ እየታዩ ይያዛሉ።

የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም የመረጃ ልውውጦች

UVACH ስለ ፕሮግራማችን እና ስለተገኝነቱ በአግባቡ ተግባቦት ላይ መደረሱን እና ግልጽ መረጃ በሰፊው ለሕዝብ መድረሱን ለማረጋገጥ ምክንያታዊ ጥረት ያደርጋል። ግለሰቦች የእኛን የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ እና ፖሊሲ በፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲዎችውስጥ ቅጂ ማግኘት ይችላሉ።  UVACH የድረ-ገጹን አድራሻ ለሚጠይቅ ለማንኛውም ግለሰብ ያቀርባል። ግለሰቦች በተጨማሪም የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻውን ለማግኘት እና እሱን ለማጠናቀቅ እርዳታ ለመቀበል ከማናቸውም የመመዝገቢያ አካባቢዎች፣ የፋይናንስ አማካሪዎች እና የገንዘብ ያዥ ቢሮዎች ማግኘት ይችላሉ። የገንዘብ ነክ አማካሪዎች ወይም የገንዘብ ያዥ ቢሮዎች በታካሚ መመዝገቢያ አካባቢዎች ውስጥ ይገኛሉ። ግለሰቦች በእያንዳንዱ ሆስፒታል ውስጥ በማንኛውም የመረጃ ዴስኮቻችን ላይ የገንዘብ ነክ አማካሪን ወይም የገንዘብ ያዥ ቢሮዎች የት እንዳሉ ቆም ብለው መጠየቅ ይችላሉ። ግለሰቦች የእናን የገንዘብ እገዛ ማመልከቻ እና የፖሊሲ ቅጅዎች በመጻ በፖስታ መልዕክት፣ እንዲሁም ለCPMC የደንበኞች አገልግሎት ክፍል በስልክ ቁጥር 540-829-4320 ወይም 540-829-4330 (የአገር ውስጥ) በመደወል ማግኘት ይችላሉ። የPWMC እና HAMC የደንበኞች አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 703-369-8020 (PWMC) ወይም 571-284-1517 (HAMC) ላይ ሊገኝ ይችላል።