የሂሳብ አከፋፈል እና የስብስብ መመሪያ Billing & Collections Policy, Amharic (Ethiopia)

Make an Appointment
For the Charlottesville area:
For Manassas or Haymarket:

ርዕስ፦                

ክፍያ መጠየቅ እና መሰብሰብ\          

ቀን፦                  

08/26/2022

የታደሰው በ 03/01/2023

ምድብ፦              

የታካሚ የፋይናንስ አገልግሎቶች      

የጸደቀው በ፦ UVACH Inc. ቦርድ

 

ዓላማ

የዚህ ፖሊሲ ዓላማ ለUVA Community Health (UVACH) የክፍያ መጠየቅና አሰባሰብ ልማዶችን በተመለከተ መረጃ ማቅረብ ሲሆን፣ ይኽም UVA Health Culpeper Medical Center (CPMC)፣ UVA Health Haymarket Medical Center (HAMC)፣ UVA Health Prince William Medical Center (PWMC)፣ UVACH Medical Group፣ እና UVA Health Cancer Center Gainesville ያካትታል። (ከዚህ በኋላ “የማኅበረሰብ ጤና አካላት” (Community Health entities) ተብለው ይጠቀሳሉ)

ተፈጻሚነት

ይህ ፖሊሲ በሁሉም የማኅበረሰብ ጤና አካላት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። የማኅበረሰብ ጤና አካላትን በመወከል የሚሰራ ማንኛውም ሰብሳቢ ኤጀንሲ ከታች የተገለጹትን የአሰባሰብ ልማዶች ያከብራል እንዲሁም ይደግፋል። በግልጽ ካልተቀመጠ በስተቀር፣ ይህ ፖሊሲ በሐኪሞች ወይም በሌሎች የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፣ ይኽም በማኅበረሰብ ጤና የሕክምና ቡድን (Community Health Medical Group) ያልተቀጠሩ የድንገተኛ ክፍል
ሐኪሞችን፣ አንስቴዢዮሎጊስቶችን፣ ራዲዮሎጂስቶችን፣ ሆስፒታሊስቶችን እና ፓቶሎጆስቶችን የሚያካትት ሲሆን፣
በእነዚህ የተገደበ አይሆንም።

ብያኔዎች

በአጠቃላይ የሚጠየቁ መጠኖች (Amounts Generally Billed (AGB))፦ በአጠቃላይይ የሚጠየቁ መጠኖች ማለት እንዲህ ላሉ አገልግሎቶች መድን ያላቸው ታካሚዎች ለድንገተኛ ሕክምና እና አስፈላጊ ለሆኑ የሕክምና አገልግሎቶች በአጠቃላይ የሚጠየቁት መጠን ነው። የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ የሆኑ ታካሚዎች የሚጠየቁት ክፍያ እንዲህ ላሉ አገልግሎቶች በአጠቃላይ ከሚጠየቁ መጠኖች (“AGB”) ያልበለጠ መሆን አለበት። እነዚህ ክፍያዎች፣ ከሜዲኬር እና ከንግድ ዋሶች ለድንገተኛ ሕክምና እና አስፈላጊ ለሆነ ሕክምና የተፈቀደው መጠን አማካይ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የተፈቀዱት መጠኖች መድን አቅራቢው የሚከፍለውን መጠን እና ግለሰቡ በግል መክፈል ያለበት መጠን ካለ እርሱንም ያካትታል። CPMC፣ PWMC እና HAMC AGBs በ 26 CFR §1.501(r). ያለፈውን በማየት ይሰላሉ።

የተበላሸ ዕዳ- መሰብሰብ እንደማይችሉ ተቆጥረው የተሰረዙ ያልተከፈሉ ገቢዎች፤ ነገር ግን እንደ ተከፋይ ዕዳ ተመዝግበው ያሉ።

ሰብሳቢ ኤጀንሲ- ሰብሳቤ ኤጀንሲ ማለት ክፍያዎችን ከዋሶች በመሰብሰብ ተግባር ላይ የተሰማራ ማንኛውም አካል ነው።

የብቁነት ጊዜ- ለዋሱ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጥበት የጊዜ ክልል ነው።

መደበኛ ያልሆነ የመሰብሰብ እርምጃ (ECA)- ECA ማለት ከሚከተሉት አንዱ ነው፦

  • አንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው፣ የአንድን ግለሰብ ዕዳ ለሌላ ሰው መሸጥ
  • ለክሬዲት መዝጋቢ ኤጀንሲዎች ወይም የክሬዲት ቢሮዎች የክስ ሪፖርት ማቅረብ
  • ቀድሞ ለቀረበው ሕክምና ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት፣ አስፈላጊ የሆነ ሕክምናን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ፣ መከልከል ወይም አገልግሎት ከማግኘታቸው በፊት ውዝፋቸውን እንዲከፍሉ መጠየቅ።
  • ሕጋዊ ሂደት የሚጠይቁ እርምጃዎች፣ የሚከተሉትን አካትቶ ነገር ግን በእነርሱ ሳይወሰን፦
    • በንብረት ላይ ውርስ ማወጅ
    • የቤት ንብረትን በሃራጅ መሸጥ
    • የባንክ ሂሳብን ወይም ሌላ የግል ንብረትን ማሳገድ ወይም መያዝ
    • በግለሰብ ላይ የፍትሐብሄር ክስ መመስረት
    • ግለሰብን ማሳሰር
    • ግለሰብን በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳገድ
    • ተቆራጭ ማሳዘዝ

በክስረት ሂደት ውስጥ ይገባኛል ማመልከት ከመደበኛ ውጭ የሆነ የመሰብሰብ እርምጃ አይደለም።

ዋስ- ታካሚው፣ ሕክምና አቅራቢው፣ ወይም ለጤና ሕክምና ክፍያ ኃላፊነት ያለበት አካል።

የታካሚ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም (Patient Financial Assistance Program)- ዋሱ ያለበትን ዕዳ ለመቀነስ ታስቦ የተነደፈ ፕሮግራም። ይህ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲያችን ውስጥ በተገለጸው መሰረት የብቁነት መመዘኛዎችን ለሚያሟሉ ዋሶች የሚቀርብ ፕሮግራም ነው።

የታካሚ ኃላፊነት የመድን ሽፋን ላላቸው ታካሚዎች- የታካሚ ኃላፊነት የመድን ሽፋን ላላቸው ታካሚዎች ማለት፣ የታካሚው ሶስተኛ-ወገን ሽፋን የታካሚውን የድጎማ ገደብ ከወሰነ በኋላ ታካሚው ከኪሱ አውጥቶ መክፈል የሚጠበቅበት መጠን ሲሆን፣ የጋራ ክፍያዎችን፣ የጋራ መድንን እና ተቀናናሾችን ያካትታል።

የታካሚ ኃላፊነት የመድን ሽፋን ለሌላቸው ታካሚዎች- አንድ ታካሚ፣ ማናቸውም የመድን ሽፋን ለሌላቸው የሚቀርቡ ተቀናሾች ከተተገበሩ በኋላ፣ መክፈል የሚጠበቅበት መጠን ነው።

ሶስተኛ-ወገን ከፋይ- የግለሰብ ጤና አገልግሎቶች ክፍያዎችን ለመሸፈን ተሳታፊ የሆነ፣ ከታካሚው (የመጀመሪያው ወገን) ወይም ከጤና ክብካቤ አቅራቢው (ሁለተኛ ወገን) ሌላ የሆነ አካል።

በቂ የመድን ሽፋን የሌለው- የመድን ሽፋን ያለው ነገር ግን ሽፋን ለሌላቸው አገልግሎቶች በድጎማ ዕቅዱ መሰረት ክፍያ የሚጠየቅ ግለሰብ። ለምሳሌ በእነርሱ ሳይገደብ የሚከተሉትን ያካትታል፦ የሜዲኬር በራስ የሚወሰዱ መድሃኒቶች፣ ከፍተኛው ገደባቸው ላይ የደረሱ ድጎማዎች፣ የወሊድ ምድን፣ ወዘተ

የመድን ሽፋን የሌለው- የመድን ሽፋን የሌላቸው ታካሚዎች፦

 

ፖሊሲ

ዋሶችን እና ተፈጻሚነት ያላቸው ሶስተኛ-ወገኖችን በትክክል፣ በወቅቱ፣ እና በወጥነት፣ ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች እና መመሪያዎች መሰረት ማስከፈል የUVA የማኅበረሰብ ጤና አካላት ፖሊሲ ነው።

በዝርዝር የተቀመጠ መግለጫ

ዋሶች ለሂሳባቸው በማንኛውም ጊዜ፣ ያለ ተጨማሪ ክፍያ፣ በዝርዝር የተቀመጠ መግለጫ ሊጠይቁ ይችላሉ።

መቃወሚያዎች

ማንኛውም ዋስ አንድን ነጠላ ክፍያ ወይም በክፍያ መጠየቂያ ላይ ያላቸውን መጠን መቃወም ይችላሉ። ዋሶች ተቃውሟቸውን በጽሁፍ ወይም በስልክ ለደንበኞች አገልግሎት ወኪል ማቅረብ ይችላሉ። አንድ ዋስ የክፍያ መጠየቂያቸውን አስመልክተው ሰነድ ቢጠይቁ፣ የተቋሙ ሰራተኛ የተጠየቀውን ሰነድ ለዋሱ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ለማቅረብ ምክንያታዊ ጥረት ያደርጋል።

የክፍያ ክፍለ ጊዜ

የማኅበረሰብ ጤና አካላት የክፍያ ክፍለ ጊዜ ከመጀመሪያው መግለጫ ቀን ይጀምራል እንዲሁም ከዚያ ቀን ከ120 ቀናት በኋላ ያበቃል። በክፍያ ክፍለ ጊዜ ወቅት ዋሶች የስልክ ጥሪዎች፣ መግለጫዎች እና ደብዳቤዎች ሊደርሷቸው ይችላሉ። በሙሉው የክፍያ ክፍለ ጊዜ ወቅት ዑደት ውስጥ ለዋስ ስልክ ሊደወል ይችላል። ከዚህ በታች ያለው የመግለጫዎች እና ደብዳቤዎች
የጊዜ ሰሌዳ ነው፦

  • ዋሱ ያልተከፈለ ቀሪ ሂሳብ እንዳለበት ከተረጋገጠ በኋላ የሂሳብ መግለጫ ለዋሱ ይላካል
  • የሂሳብ መግለጫው ከተላከ ከ30 ቀናት በኋላ ለዋሱ ክፍያቸው ጊዜው እንዳለፈ የሚገልጽ የክትትል ደብዳቤ ይላካል
  • የመጀመሪያው ደብዳቤ ከተላከ ከ30 ቀናት በኋላ ለዋሱ ክፍያቸው መበላሸቱን የሚገልጽ ሁለተኛ ደብዳቤ ይላካል
  • ሁለተኛው ደብዳቤ ከተላከ ከ30 ቀናት በኋላ ለዋሱ ሂሳባቸው በከፍተኛ ደረጃ እንደተበላሸና ሂሳቡ ለሰብሳቢ ኤጀንሲ ሊተላለፍ እንደሆነ የሚገልጽ ሶስተኛ እና የመጨረሻ
  • ደብዳቤ ይላካል።
  • በክፍያ ክፍለ ጊዜው 120ኛ ቀን የዋሱ ሂሳብ ለሰሳቢ ኤጀንሲ ይተላለፋል።

በክፍያ ክፍለ ጊዜው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ የሂሳብ መግለጫ እና ደብዳቤ ስለ ክፍያ ዘዴዎች፣ ክፍያ አማራጮች፣ የገንዘብ ድጋፍ ድር ጣቢያ፣ እና የደንበኞች አገልግሎት ስልክ ቁጥርን ያካትታል።

 

አሰራር

ለዋስ ያልሆነ የክፍያ መጠየቂያ

  1. የሽፋን መረጃ ማግኘት፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት፣ የግል ወይም የሕዝብ የጤና መድን በከፊልም ሆነ በሙሉ፣ በሆስፒታሉ ለታካሚው ለቀረቡ አገልግሎቶች ክፍያዎችን ይሸፍን እንደሆነ ከታካሚዎች መረጃ ለማግኘት ምክንያታዊ ጥረት ያደርጋሉ።
  2. የሶስተኛ-ወገን ከፋዮችን ክፍያ መጠየቅ፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት ከሶስተኛ-ወገን ከፋዮች የሚጠበቁ ሁሉንም ክፍያዎች በትጋት መሰብሰብ አለባቸው፣ ይኽም በነርሱ ሳይገደብ፣ በኮንትራት ወይም ያለ ኮንትራት የሚከፍሉ ከፋዮች፣ የዋስትና ከፋዮች፣ የቀጥታ የታካሚ ሽፋን የሚያቀርቡ የኃላፊነት እና የአውቶሞቢል መድን አቅራቢዎች፣ እንዲሁም ለታካሚው ሕክምና ኃላፊነት ያለባቸው የመንግስት ፕሮግራም ከፋዮችን ያካትታል። በተጨማሪም፣ የማኅበረሰብ ጤና አካላት ሁሉንም ተፈጻሚነት ያላቸው የሶስተኛ-ወገን ከፋዮችን በታካሚው ወይም በወኪላቸው በቀረበ ወይም በተረጋገጠ መረጃ መሰረት ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ክፍያ ይጠይቃሉ።

 

ለዋስ የሆነ የክፍያ መጠየቂያ

በተከታታይ የሚላክ የሂሳብ መግለጫ እና ደብዳቤ ዋሱ መክፈል ያለበትን መጠን በተመለከተ መረጃ ለመስጠት ያገልግላሉ። እያንዳንዱ የሂሳብ መግለጫ እና ደብዳቤ ስለ ክፍያ ዘዴዎች፣ ክፍያ አማራጮች፣ የገንዘብ ድጋፍ ድር ጣቢያ፣ እና የደንበኞች አገልግሎት ስልክ ቁጥርን ያካትታል።

  1. የመድን ሽፋን ያላቸውን ታካሚዎች ክፍያ መጠየቅ፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት ዋሱን ወዲያውኑ የተጠቀሰውን መጠን መጠየቅ አለባቸው። ይኽም መጠን በድጎማዎች መግለጫ (Explanation of Benefits (EOB)) ወይም በድጎማ አወቃቀር መሰረት የሚመራ ወይም የሚወሰን ነው።
  2. የመድን ሽፋን የሌላቸውን ታካሚዎች ክፍያ መጠየቅ፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት፤ የመድን ሽፋን የሌላቸውን ተቀናሾች ከተገበሩ በኋላ ዋሱ ያለበትን የክፍያ መጠን ወዲያውኑ መጠየቅ አለባቸው።

የአሰባሰብ ልማዶች

1. አጠቃላይ የአሰባሰብ ልማዶች፦ በዚህ ፖሊሲ መሰረት፣ የማኅበረሰብ ጤና አካላት፣ ከዋሶች ክፍያዎችን ለማግኘት፣ ምክንያታዊ የአሰባሰብ ጥረቶችን ሊያደርጉ ይችላሉ። አጠቃላይ የአሰባሰብ እንቅስቃሴዎች የዋስ የሂሳብ መግለጫዎችን/ደብዳቤ መላክ፣ የስልክ ጥሪዎች፣ እንዲሁም ሂሳቦችን በእነርሱ ሳይገደብ፣ ለቅድመ ስብስባ፣ ለቀድሞ ወጪ እና ለተበላሹ ዕዳዎች ሻጮች ለመሳሰሉ የንግድ አጋሮች ማስተላለፍን ያካትታሉ።

2. መደበኛ ያልሆኑ የመሰብሰብ እርምጃዎች፦ የማኅበረሰብ የጤና አካላት እና የሰብሳቢ ኤጀንሲ አጋሮች በክሬዲት ቢሮ ሪፖርት አደራረግ መልክ በፌዴራል ፍትሐዊ የዕዳ አሰባሰብ ልማዶች ሕግ (Federal Fair Debt Collection Act) መሰረት ያሉበትን ግዴታዎች በማክበር ECAን ሊተገብሩ ይችላሉ። የክፍያ ክፍለ ጊዜ ካበቃ በኋላ ያሉት 60 ቀናት ከማለፋቸው በፊት አንድን ዋስ ያለበትን ዕዳ ባለመክፈሉ ለክሬዲት ቢሮ ሪፖርት ማድረግ አይቻልም። አንድ ዋስ ለክሬዲት ቢሮ ሪፖርት ከመደረጉ ከ30 ቀናት በፊት በሰብሳቢ ኤጀንሲው አማካይነት እንዲያውቀው ይደረጋል። የማኅበረሰብ ጤና አካላትም ሆኑ ሰብሳቢ ኤጀንሲ አጋሮቻቸው ዋሶች ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ ይሆኑ እንደሆነ ለማወቅ ምክንያታዊ ጥረት ከማድረጋቸው በፊት ወደ ECA ማምራት የለባቸውም።

3. ምንም አይነት ECA በገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ሂደት ወቅት አይኖርም፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት እና ሰብሳቢ ኤጀንሲ አጋሮቻቸው ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ባስገባ ዋስ ላይ ECA ማከናወን የለባቸውም። ዋሱ ለገንዘብ ድጋፍ መስፈርቶቹን የምያሟላ ሆኖ ከተገኘና ዋሱ ገንዘብ የከፈለ ከሆነ፣ የማኅበረሰብ ጤና አካላት ከ$5.00 በላይ የሆነን ማንኛውንም ዋሱ ብቁ በሆነበት ወቅት የከፈለን ገንዘብ ተመላሽ ያደርጋሉ። ዋሱ ከፊል የገንዘብ ድጋፍ የተፈቀደለት ከሆነ፣ የማኅበረሰብ ጤና አካላት ዋሱ በግሉ መክፈል ከሚጠበቅበት በላይ የከፈለውን ማንኛውንም መጠን ተመላሽ ያደርጋሉ። የማኅበረሰብ ጤና አካላት ከ$5 በታች የሆነን ማንኛውንም መጠን ለዋሱ
ተመላሽ አያደርጉም።

4. የክፍያ ዕቅዶች

  • ብቁ ታካሚዎች፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት እና እነርሱን በመወከል የሚሰራ ማንኛውም ሰብሳቢ ኤጀንሲ ለዋሶች ወደ ክፍያ ዕቅድ ስምምነት የመግባት አማራጭን ማቅረብ አለበት። የክፍያ ዕቅድ ስምምነቱ ዋሱ ያለበትን ዕዳ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍሎ እንዲጨርስ ይፈቅዳል።
  • የክፍያ ዕቅድ ደንቦች ፦
    • ሁሉም የክፍያ ዕቅዶች ከወለድ ነጻ መሆን አለባቸው
    • ሁሉም ወርሃዊ ክፍያዎች በማኅበረሰብ ጤና አካላት እና በዋሱ መካከል ስምምነት ላይ በተደረሰበት መጠን የሚፈጸሙ መሆን አለባቸው።
    • ያልተከፈለ ውዝፍ ሂሳብ ስምምነት በተደረሰበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተከፍሎ ማለቅ አለበት
  • የክፍያ ዕቅድ የተበላሸ መሆኑን መበየን፦ የክፍያ ዕቅድ የተበላሸ ነው የሚባለው ዋሱ ሁሉንም ተከታታይ ክፍያዎች ሳይከፍል ከቀረ ነው። ይህ ከተከሰተ፣ ዋሱ የተበላሸ ዕዳ ማሳወቂያ ይደርሰዋል። ማሳወቂያው ለዋሱ በመጨረሻ የታወቀ አድራሻ ይላካል። አንድ የክፍያ ዕቅድ የተበላሸ መሆኑ ከተበየነ በኋላ፣ የማኅበረሰብ ጤና አካላት ወይም ሰብሳቤ ኤጀንሲ፣ በዚህ ፖሊሲ ውስጥ በተጠቀሰው አግባብ መሰረት የመሰብሰብ እንቅስቃሴዎችን መጀመር ይችላል።

5. ሰብሳቢ ኤጀንሲዎች፦ የማኅበረሰብ ጤና አካላት የዋስ ሂሳቦችን፣ በሚከተሉት ሁኔታዎች መሰርት ለሰብሳቢ ኤጀንሲ ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

  • ሰብሳቢ ኤጀንሲው ከማኅበረሰብ ጤና አካላት ጋር በጽሁፍ የተቀመጠ ስምምነት ያለው መሆን አለበት።
  • በጽሁፍ የተቀመጠው ከሰብሳቢ ኤጀንሲው ጋር የተደረገ ስምምነት ሰብሳቢ ኤጀንሲው የማኅበረሰብ ጤና አካላትን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ዋና እሴቶች፣ የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲውን ደንቦች እና ይህን የክፍያ መጠየቅ እና መሰብሰብ ፖሊሲ የሚያከብር መሆኑን የሚጠቅስ ቋንቋ ያካተተ መሆን አለበት።
  • ሰብሳቢ ኤጀንሲው ማናቸውንም ECAዎች ከመጀመሩ ከ30 ቀናት በፊት ልዋሱ ማሳወቅ አለበት። ይህ ማሳወቂያ የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲውን ቀላል ገጽ መግለጫ ያካተተ መሆን አለበት።
  • የማኅበረሰብ ጤና አካላት ዕዳውን የራሳቸው አድርገው ማቆየት አለባቸው (ይኽም ማለት፣ ዕዳው ለሰብሳቢ ኤጀንሲው “አይሸጥም”)።
  • ሰብሳቢ ኤጀንሲው የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት መመዘኛዎቹን የሚያሟሉ ዋሶችን የሚለይበት አሰራር ያለው መሆን አለበት። ሰብሳቢ ኤጀንሲው የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም መኖሩን ማሳወቅ እና የገንዘብ ድጋፍ የሚፈልጉ ዋሶችን
    በስልክ ወይም በድር ጣቢያ አማካኝነት ወደ ማኅበረሰብ ጤና አካላት መልሶ መላክ አለበት። https://uvahealth.com/services/billing-insurance/financial-assistance-eligibility. የማኅበረሰብ ጤና አካላት እና ሰብሳቢ ኤጀንሲ አጋሮቻቸው ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ባስገባ ዋስ ECA ማከናወን የለባቸውም።
  • የማኅበረሰብ ጤና አካላት የመጀመሪያውን የክፍያ መጠየቂያ ለዋሱ ከላኩ በኋላ ቢያንስ 120 ቀናት ሳያልፍ፣ ተመላሽ የሆነ ደብዳቤ ካልደረሰ እና ወቅታዊውን አድራሻ ለማግኘት ምክንያታዊ ጥረት ሳይደረግ ማንኛውም ቀሪ ሂሳብ ወደ ሰብሳቢ ኤጀንሲ መተላለፍ የለበትም።
  • ዋሱ የአከፋፈል ዕቅድ ላይ በመደራደር ላይ ካለ ወይም ክፍያው ያልተበላሸ ከሆነ ማንኛውም ቀሪ ሂሳብ ወደ ሰብሳቢ ኤጀንሲ መተላለፍ የለበትም።