UVA Health እና UVA Community Health (UVACH) ተልእኮ፣ ይህም UVA Health Culpeper Medical Center (CPMC)፣ UVA Health Haymarket Medical Center (HAMC)፣ UVA Health Prince William Medical Center (PWMC)፣ UVACH የሕክምና ቡድን እና UVA Health የካንሰር ማዕከል Gainesville፣ የመክፈል አቅማቸው ምንም ይሁን ምን ርህራሄ፣ ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት ነው። UVA Helath ከማንኛውም የሆስፒታላችን ፋሲሊቲ እና/ወይም ተቀጥረው የሚሰሩ አቅራቢዎች ድንገተኛ ወይም ሌላ የሕክምና አስፈላጊ እንክብካቤ ለሚያገኙ ታካሚዎች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል።
ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ የሆነው ማነው?
UVA Health የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲ "FAP" አመታዊ ጠቅላላ የቤተሰብ ገቢያቸው አሁን ካለበት የፌደራል የድህነት ደረጃ (FPL) 200% ወይም ከዛ በታች እና የንብረት ደረጃ 50,000 ዶላር ወይም ከዛ በታች ለሆኑ ታካሚዎች ለድንገተኛ ጊዜ ወይም ለሌላ የሕክምና አስፈላጊ እንክብካቤ 100% የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል። ዋና መኖሪያ ከሆነ ለተሽከርካሪዎች እና ለሪል እስቴት የተወሰኑ ነፃነቶች አሉ። እንዲሁም UVA Health የቤተሰብ አጠቃላይ ገቢያቸው ከ FPL 201% እና 400% መካከል ላሉ እና የንብረት ደረጃ 50,000 ዶላር ወይም ከዛ በታች ለሆኑ ታካሚዎች ቅናሽ ይሰጣል።
ለገንዘብ ድጋፍ እንዴት ማመልከት ይቻላል?
ለድንገተኛ እና ለሕክምና አስፈላጊ እንክብካቤ የመክፈል አቅማቸው የሚያሳስባቸው ግለሰቦች የገንዘብ ድጋፍ ሊጠይቁ ይችላሉ። ለገንዘብ ድጋፍ ለማመልከት፣ ታካሚው ወይም በገንዘብ ሀላፊነት ያለው አካል፣ የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻችንን መሙላት አለባቸው። የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ እና የ FAP ቅጂዎች ለደንበኞች አገልግሎት ክፍል በ 866-320-9659 በመደወል በፖስታ በነፃ ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም፣ የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ እና የ FAP ቅጂ ከድረ-ገጻችን https://uvahealth.com/services/billing-insurance/financial-assistance-information በማውረድ በነፃ ማግኘት ይቻላል።
ምን አገልግሎቶች ይሸፈናሉ?
የተመላላሽ ታካሚ አገልግሎቶችን፣ የታካሚ እንክብካቤን እና የድንገተኛ ክፍል አገልግሎቶችን ጨምሮ ሁሉም ድንገተኛ ወይም ሌሎች ለሕክምና አስፈላጊ አገልግሎቶች በ FAP ስር ይሸፈናሉ። ብቁ-ያልሆኑ አገልግሎቶች እንደ፣ በተመረጡ የሕክምና አስፈላጊ-ያልሆኑ ሂደቶች፣ የመዋቢያ እና ጠፍጣፋ ዋጋ ሂደቶች፣ ረጅም ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የመድን ዋስትና ያላቸው ታካሚዎች መድናቸውን ላለመጠቀም የመረጡ እና በአደጋ ምክንያት የሚሰጡ አገልግሎቶች በገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም አይሸፈኑም። በአደጋ ምክንያት የሚሰጡ አገልግሎቶች በሶስተኛ ወገን ካልተሸፈኑ ታካሚዎች ለገንዘብ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ። ከመድን በኋላ ቀሪ ሂሳብ በሚኖር ጊዜ፣ ታካሚው ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላል። በገቢ ገደብ ውስጥ ያሉ መድን ያላቸው ታካሚዎች በመድን ኩባንያው መካከል ካለው ውል ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ለገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ። በ UVA Health ያልተቀጠሩ እና በሆስፒታሉ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ የዶክተሮች እና የስፔሻሊስቶች ክፍያ የ UVA Health የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራምን ላያከብረው ይችላል። ከዶክተርዎ ጋር መወያየት አለቦት ወይም የኛን ድረ-ገጽ በ https://uvahealth.com/services/billing-insurance/financial-assistance-information ላይ ለሚሳተፉ እና በ UVA Health የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም ውስጥ የማይሳተፉ አቅራቢዎች ዝርዝርን ይጎብኙ።
ጥያቄዎች ካሉኝ ወይም ማመልከቻውን ለመሙላት ድጋፍ ካስፈለገኝስ?
የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻን ለመሙላት እርዳታ የሚፈልጉ ግለሰቦች ከላይ በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች ወደ የደንበኞች አገልግሎት ክፍል በመደወል ወይም በሆስፒታሎቻችን ውስጥ በታካሚዎች ተደራሽ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኘውን የገንዘብ አማካሪን መጎብኘት ይችላሉ
- በ 1240 Lee Street, Charlottesville, VA 22903 በአካል ተገኝተው ይጎብኙ
- በ 8650 Sudley Rd, Manassas, VA 20110 በአካል ተገኝተው ይጎብኙ
- በ 15225 Healthcote Boulevard, Haymerket, VA 20169 በአካል ተገኝተው ይጎብኙ
- በ 501 Sunset Lane, Culpeper, VA 22701 በአካል ተገኝተው ይጎብኙ
እንግሊዘኛ-ተናጋሪ ላልሆኑ ታካሚዎች፣ የ FAP እና የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ትርጉሞች፣ እንግሊዝኛ እና ስጳንኛ ጨምሮ በሌሎች ቋንቋዎች ይገኛሉ። እባክዎን ከላይ ባሉት ቁጥሮች ይደውሉ ወይም ድህረ ገጻችንን ከዚ በታች ባለው ይጎብኙ፦ ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ ነዎት?| የ UVA Health የዚህን ግልጽ ቋንቋ ማጠቃለያ፣ FAP እና የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻን ትርጉሞችን ለማውረድ።